ቀጥታ፡

በአሜሪካ መንግስት ጉዳይ አስፈጻሚ ትሬሲ አን ጃኮበሰን የተመራ ልዑክ በቱሪዝም ፍሰትና ሌሎች ጉዳዮች ለመወያየት ጎንደር ከተማ ገባ

ጎንደር ሐምሌ 12/2014(ኢዜአ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ጉዳይ አስፈጻሚ ትሬሲ አን ጃኮበሰን የተመራ ልዑክ የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃትና በሌሎች ጉዳዮች ለመወያየት ጎንደር ከተማ ገብቷል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ጉዳይ አስፈጻሚ ትሬሲ አን ጃኮበሰን የተመራው የልኡካን ቡድን በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

የልኡካን ቡድኑን በአጼ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል ያደረጉለት የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ናቸው፡፡

May be an image of 8 people, people standing and outdoors

የልኡካን ቡድኑ በቆይታው ከከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጋር የከተማውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃትና ለመደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በአካባቢው በነበረው የሰላም እጦት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ በማቋቋምና በልማት ስራዎች ዙሪያ ከአካባቢው አመራሮችና ማህበረሰቡ ጋር የልኡካን ቡድኑ ውይይት እንደሚያደርግም ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም