አዲስ የተመረጠው የመጅሊስ አመራር ከቀድሞ የመጂሊሱ አመራሮች የቢሮ ቁልፍ ተረከበ - ኢዜአ አማርኛ
አዲስ የተመረጠው የመጅሊስ አመራር ከቀድሞ የመጂሊሱ አመራሮች የቢሮ ቁልፍ ተረከበ

ሐምሌ 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) አዲስ የተመረጠው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) አመራር ከቀድሞ የመጂሊሱ አመራሮች የቢሮ ቁልፍ ተረከበ።
አዲስ የተመረጡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸኸ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በርክክቡ ስነ-ስርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ከህዝበ ሙስሊሙ የተሰጣቸውን አደራ ለመወጣት ጠንክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ህዝብ ሙስሊሙ አንድነትነቱን በማጠናከር የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት መጠበቅ እንዳለበትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለማጠናከር አበክረው እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።
ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤