ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአመራሮች ምርጫ እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአመራሮች ምርጫ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥና አንድነት 2ኛ ዙር አገር አቀፍ ጉባኤ ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።

በጉባኤው ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን መጂሊሱን ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የሚመሩ አመራሮች ምርጫም በመካሄድ ላይ ነው።

በጉባኤው ላይ በድምፅ ይሳተፋሉ ተብለው ከሚጠበቁት 300 ተሳታፊዎች መካከል ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 261ዱ መገኘታቸው ታውቋል።

ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በተካሄደው ጉባኤ ከተሳተፉት መካከል 39ኙ በሞት፣ በህመም፣ ከሀጂ ጉዞ ባለመመለስና በልዩ ልዩ ምክንያቶች በዛሬው ጉባኤ አለመገኘታቸውም እንዲሁ።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥና አንድነት 1ኛ ዙር አገር አቀፍ ጉባኤ ሚያዚያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም