ቀጥታ፡

አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የሶማሌ ክልል የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብርን አስጀመሩ

ሐምሌ 11 ቀን 2014 (ኢዜአ)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ከሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ ጋር በጋራ በመሆን በጅግጅጋ ከተማ የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሀ ግብር አስጀምረዋል።

በጅግጅጋ ከተማ ዛሬ በተጀመረው የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራ 30 የአቅመ ደካማ ዜጎች እድሳት ተደርጓል።

እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ የተከናወነ ሲሆን በዚሁ ወቅት በሚኒስትር ማዕረግ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ እንዳሉት የአለም አየር ንብረት ለውጥ መዛባት የተከሰተው በደን መመናመን እንደመሆኑ የአረንጓዴ አሻራ መካሄዱ ከፍተኛ አስተዋፆ አለው።

በተለይም ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።

አያይዘውም እንደ ሶማሌ ክልል ባሉ ድርቅ የተከሰተባቸው አካባቢዎች እንዲያገግሙ ሚናው የጎላ ነው ያሉት።የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህሉን የሚያጎለብት መሆኑንም ገልፀዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ ተቋማት አባላትና አመራሮች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም