ቀጥታ፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጅግጅጋ ገቡ

ጅግጅጋ፤ ሐምሌ 11/2014 (ኢዜአ)፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና የየዴሞክራሲ ተቋማት ኃላፊዎችና ሚኒስትሮች ጅግጅጋ ገቡ።

አፈ- ጉባኤ  አቶ ታገሰ ጫፎና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች  ጅግጅጋ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማንና  የክልል ቢሮ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።

የህዝብ ተወክዮች ምክር ቤት ተጠሪ ተቋማት አባላትና አመራሮች በነገው እለት በጅግጅጋ ከተማ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ነዋሪዎች የቤት እድሳት፣ ጥገና ስራና የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር  እንደሚያከናውኑ ይጠበቃል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም