ቀጥታ፡

በደቡብ ዕዝ የሚገኘው ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ከየትኛውም አቅጣጫ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ለመመከት ዝግጁ ነው-ሜጄር ጀኔራል ናስር አባዲጋ

ሐምሌ 08 ቀን 2014(ኢዜአ) በደቡብ ዕዝ የሚገኘው የሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ከየትኛውም አቅጣጫ ሊቃጣ የሚችልን ጥቃት ለመመከት በሚያስችል የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ።

የሜካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ሜጄር ጀኔራል ናስር አባዲጋ እንደተናገሩት በየትኛውም ጊዜና ሰዓት መንግስት በሚሰጠን ትዕዛዝ መሰረት አሸባሪም ይሁን ወራሪ ኃይልን ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ በአስተማማኝ ወታደራዊ ቁመና ላይ እንገኛለን።

May be an image of 1 person, military uniform and outdoors

ዋና አዛዡ አክለውም ሜካናይዝድ ክፍለ ጦሩ ለእግረኛ ኃይላችን የተኩስ ድጋፍ ለመስጠት እና በጠላት ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁነቱን አረጋግጧል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም