የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በጅማ ከተማ ያዘጋጀው የፎቶ አውደርዕይ ተከፈተ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በጅማ ከተማ ያዘጋጀው የፎቶ አውደርዕይ ተከፈተ
ጅማ ሐምሌ 07/2014(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በጅማ ከተማ ያዘጋጀው የፎቶ አውደርዕይ ተከፈተ።
አውደርዕዩ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የሥራ ሃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ጎብኝተዋል።
የፎቶ አውደርዕዩ ከ1960ዎቹ ጀምሮ ኢትዮጵያ ያለፈችባቸውን የፖለቲካ ሂደቶች፣ ፈተናዎች እና የኢኮኖሚ እድሎችን የሚያሳይ ነው።
ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በግንባታ ስራዎች ያሉ የፈጠራ ስራዎችና እንቅስቃሴዎችን የሚያሳዩ ፎቶዎችም ለተመልካች ቀርበዋል።
በተጨማሪም በዘመኑ የነበሩ ቴፖችና ሬዲዮኖች እንዲሁም የዘመኑ ሙዚቃዎችና መዝሙሮች በምስልና በድምጽ በአውደርዕዩ ላይ ተካተዋል።
ከአውደርዕዩ ጎን ለጎን ድርጅቱ "ብሩህ ሀሳብ፣ ስራና ክህሎት ስለ ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል በጅማ ዩኒቨርሲቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያዘጋጀው ውይይት መድረክም መካሄድ ጀምሯል።
የፎቶ አውደርዕዩ ለአንድ ቀን ብቻ እንደሚቆይ ታውቋል።