ቀጥታ፡

የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ምርመራና የጥፋት ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሂደትን እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ ሀምሌ 6/2014 /ኢዜአ/ የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ምርመራና የጥፋት ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሂደትን እየገመገመ ነው።

በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች የተፈፀሙ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር እና ለተፈፀሙ ጥፋቶች የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደስራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

ግብረ ኃይሉ ዛሬ እያደረገ ባለው ሶስተኛው ስብሰባ ሁለት አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ነው።

አንደኛው ባለፉት ወራት የግብረ ኃይሉ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት የነበረውን የስራ እንቅስቃሴዎችና ተግዳሮቶች ዝርዝር ሪፖርት መገምገም ሲሆን ሁለተኛው በዓለም አቀፉ ሰብዓዊ መብትና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥምር የምርመራ ቡድን ምክረ ሀሳብ መሰረት የሽግግር ፍትሕ ማረጋገጥን በተመለከተ የተዘጋጀው ሰነድ ላይ ውይይት ማድረግ ነው።

በዚህም የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል በጦርነቱ የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም ገቢራዊነት ላይ የደረሰበትን ደረጃ እየገመገመ ነው።

የሚኒስትሮች ግብረኃይል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ታደሰ ካሳን የግብረ ኃይሉ የደረሰበትን ደረጃ ሪፖርት እያቀረቡ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም