ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ስራ አስፈፃሚና ፕሬዚዳንት እጩዎች ምዝገባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 18 ይካሄዳል

ሐምሌ 5 ቀን 2014 (ኢዜአ)የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ስራ አስፈፃሚና ፕሬዚዳንት እጩዎች ምዝገባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓም እንደሚካሄድ ምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴው አስታወቀ።

ለቀጣይ አራት ዓመታት ፌደሬሽኑን በስራ አስፈፃሚና ፕሬዚዳንትነት የሚመሩ ሰዎች ምርጫም ነሐሴ 22 ቀን 2014 ይካሄዳል።

ይህን ምርጫ የሚመራው ኮሚቴ ግንቦት 7 ቀን 2014 በተደረገው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ መመረጡ ይታወሳል።

የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባላት እየሰራቸው ያሉ ስራዎች በተመለከተ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል።

የምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሀይሉ ሞላ በዚህ ምርጫ የሚሳተፉ እጩዎች ምዝገባ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2014 ዓም ይካሄዳል።

የእጩዎች ስም ዝርዝር ደግሞ ከምዝገባው መጠናቀቅ በኋላ ባለው አንድ ሳምንት ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

በዘንድሮው ምርጫ ከዚህ በፊት እንደነበረው ምርጫውን በተመለከተ ከኮሚቴው አባላት ሙሉ እውቅና ውጭ መግለጫ መስጠት እንደማይፈቀድ ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም