በስንዴ ምርት የተገኘው እምርታ መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ማሳያ ነው-ቢልለኔ ስዩም - ኢዜአ አማርኛ
በስንዴ ምርት የተገኘው እምርታ መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ማሳያ ነው-ቢልለኔ ስዩም
ሐምሌ 5 ቀን 2014 (ኢዜአ)በስንዴ ምርት የተገኘው እምርታ የኢትዮጵያ መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ማሳያ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገለጹ ፡፡
ኋላፊዋ ይህ ያሉት በኔሽን ጋዜጣ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በየወሩ ከሚያደርጉት የልማት ክትትሎች መካከል የግብርናው ምርታማነት አንዱ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡
በስንዴ እና የተለያዩ ግብርና ምርት ላይ የተሰማሩ ገበሬዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩ ያልተቋረጠ ትኩረት፣እውቀት እና እገዛ ትልቅ ማበረታቻ እንደሆናቸው አስረድተዋል፡፡
በማሳያም በተጠናቀቀው በጀት አመት የመጀመሪያው ምዕራፍም ከ405 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት 16 ነጥብ 2 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ መመረቱን ተናግረዋል፡፡
በሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ በ208 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ 8 ነጥብ 35 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ምርት ተሰብስቧል ነው ያሉት፡፡
ይህም የስንዴ ምርትን ለማሳደግ ኢኒሼቲቩ እ.አ.አ 2018 በ3 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ላይ መጀመሩን አስታውሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ የአስር አመት የልማት እቅድ እንደ ግብርና ባሉ ቁልፍ ማርታማ ዘርፎች ላይ በማተኮር ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ላይ እንደሚያተኩር ተናግረዋል፡፡
የግብርናው ኢኮኖሚ ሀገራዊ እድገትን ከማፋጥን ባለፈ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህን አውን ለማዴረግ መንግስት በምርጥ ዘር፣መስኖና መካናይዝድ ግብርና በመታገዝ ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ ሀብት እንድትጠቀም ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያ ላለፉት በርካታ አመታት የስንዴ ምርትን ከውጭ በማስገባት ጥገኛ እንደነበረች አስታውሰው፤ ባለፉት ሁለት አመታት በተሰጠው ልዩ ትኩረት በስንዴ እራስን ከመቻል አልፎ ምርቱን ወደ ውጭ ለመላክ ጥረት እየተደረግ ነው ብለዋል፡፡