ቀጥታ፡

ኢትዮጵያን ከሶማሌላንድ የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታ 85 በመቶ ደርሷል

ሐምሌ 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያን ከሶማሌላንድ የሚያገናኘው የበርበራ-ቶጎጫሌ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 85 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል፡፡

የመንገድ ግንባታው በሚጠናቀቅበት ወቅት ኢትዮጵያን ከበርበራ ወደብ በማገናኘት ወጪ ገቢ ንግዱን የሚያሳልጥ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ የበርበራ ወደብን በመጠቀም ኢትዮጵያን ከተቀረው አለም ጋር የሚያገናኝ መውጫ መግቢያ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም መንገዱ በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል ያለውን የንግድ ምጣኔ በ30 በመቶ ይጨምረዋል ተብሏል፡፡

በሶስት ምእራፍ እንዲተናቀቅ የታቀደለትና 234 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የበርበራ-ቶጎጫሌ የመንገድ ግንባታ በፈረንጆቹ 2022 መጨረሻ ላይ እንደሚጠናቀቅ የኢንሳይድ አፍሪካ ዘገባ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም