ቀጥታ፡

ባለፉት ጥቂት ሰአታት በአዲስ አበባ የነበረው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ መሻሻል በማሳየቱ በረራዎች ተጀምረዋል-አየር መንገዱ

ሐምሌ 4 ቀን 2014 (ኢዜአ)የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ጥቂት ሰአታት በአዲስ አበባ የነበረው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ መሻሻል ማሳየቱን ተከትሎ በረራዎች መጀመራቸውን አስታወቀ።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ፀባይ ምክንያት ተቋርጠው ከነበሩት በረራዎች አብዛኛዎቹ ተጀምረዋል ነው ያለው አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉና ከኢትዮጵያ የሚነሱ በረራዎች በአብዛኛው ተጀምረዋል።

አየር መንገዱ ለደንበኞቹ ተጨማሪ መረጃዎች ማድረሱን እንደሚቀጥልም ገልጿል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም