የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስከበሩ ጀግኖቻችንን ማሰብ አለብን -ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስከበሩ ጀግኖቻችንን ማሰብ አለብን -ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

ሐምሌ 4 ቀን 2014 ( ኢዜአ)የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስከበሩ ጀግኖቻችንን ማሰብ አለብን ሲሉ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ''ጀግናን ያላከበረች ሀገር ተተኪ ጀግኖች ሊኖራት አይቻላትም'' በማለት ተናግረዋል።
አቶ ሽመልስ ይህን ያሉት ዛሬ የኮሎኔል አብዲሳ አጋ ማስታወሻ ሃውልት በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ባስመረቁበት ወቅት ነው።
በዚህም ወቅት ኮሎኔል አብዲሳ አጋ የፀረ ፋሺሽት ትግልን ለዓለም ያበሰረ ኢትዮጵያዊ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትንና ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ እየተጉ ያሉ ጀግኖች በብዛት እንዲኖረን እየሰራን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፤ዛሬ የተመረቀው የጀግናው አብዲሳ ሐውልትም መልዕክቱ ትልቅ ነው ብለዋል።
የአሁኑ ትውልድም የኢትዮጵያን ልማት በማፋጠን የጀግኖች አባቶችን ታሪክ መድገም አለብን ብለዋል።
ለዚህም የክልሉ መንግስት በሙሉ አቅም እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያን አንድነትና የህዝቦቿን ዕኩልነት፤አብሮነትና አንድነት ያፀናው የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ማስታወሻ ሃውልት በአባገዳ ማዕከል ቆሞለታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ