ቀጥታ፡

በጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት በረራዎች ላይ መስተጓጎል ተፈጥሯል-የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ሐምሌ 4 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ በተፈጠረው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ከአዲስ አበባ በሚነሱና አዲስ አበባ በሚያርፉ በረራዎች ላይ መዘግየት መፈጠሩን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው የበረራ መዘግየትና መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ደንበኞችም የተፈጠረውን ችግር ተገንዝበው አየር መንገዱ ስለሁኔታው የሚያቀርበውን መረጃ እንዲከታተሉ መጠየቁን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም