የ1 ሺህ 443ኛው ዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ - ኢዜአ አማርኛ
የ1 ሺህ 443ኛው ዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ
ሐምሌ 02 ቀን 2014 (ኢዜአ) የ1 ሺህ 443ኛው ዒድ አል አድሃ /አረፋ/ በዓል በመላው ሀገራችን ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ህዝቡን ከጎኑ በማሰለፍና ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ጋር በመቀናጀት በዓሉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ የህዝቡን ፀጥታና ደህንነት የማስከበር ስራውን በብቃት መወጣቱን ገልጿል።
የፖሊስ ሰራዊት አባላቱ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ከራሳቸው በፊት ህዝቡን በማስቀደም የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት በመወጣት የታለመውን ግብ ማሳክት መቻሉን ፖሊስ አስታውቋል።
ከፖሊስ የተሰጠውን መግለጫ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ መላው የሀገሪቱ ህዝብና የፀጥታና ደህንነት አካላት ላደረጉት ቀና ትብብርና ድጋፍ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል።