ኢትዮጵያ የፎሬንሲክ ዲ ኤን ኤ ምርመራን በሀገር ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የፎሬንሲክ ዲ ኤን ኤ ምርመራን በሀገር ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች

ሐምሌ 02 ቀን 2014(ኢዜአ) ኢትዮጵያ የፎሬንሲክ ዲ ኤን ኤ ምርመራን በሀገር ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች።
የፎሬን ሲክ ዲ ኤን ኤ ምርመራ ላብራቶሪ በኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ስራውን ዛሬ ጀምሯል።ላብራቶሪው እጅግ ዘመናዊና ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የሚጠቀም መሆኑም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ የዲ ኤን ኤ ፎሬንሲክ የምርመራ ላብራቶሪው በሀገር ውስጥ ስራ መጀመሩ የፍትህ ስርዓቱ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ሚናው የላቀ ነው።
የፖሊስ የምርመራ አቅምን በይበልጥ ለማሳደግ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
ከዚህ ቀደም በውጭ ሀገር ለዲ ኤን ኤ ምርመራ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ የሚያስቀር እንደሆነም አክለዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ