ቀጥታ፡

1443 ኛው የኢድ አል አድሀ( አረፋ ) በዓል እየተከበረ ነው

ሐምሌ 2 ቀን 2014(ኢዜአ) 1443ኛው የኢድ አል አድሀ( አረፋ ) በዓል እየተከበረ ይገኛል::

በአዲስ አበባ እየተከበረ ባለው በዓል የሶላት ስነ ስርአት ላይ የሚታደሙ የእምነቱ ተከታዮች ትንሿ ስታዲየም እየገቡ ነው::

በአሁኑ ወቅት በስታዲየሙ ምስጋና የሚቀርብበት ተክቢራ እየተደረገ ሲሆን ተክቢራው እንደተጠናቀቀም የሶላት ስነ ስርዓት የሚካሄድ ይሆናል::

አማኞች ከሶላት በሁዋላ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ እርድ በማካሄድ እና ለሌላቸው በማካፈል በዓሉን ያሳልፋሉ::

1443ኛው የኢድ አል አድሀ( አረፋ ) በዓል በመላው አለም በእስልምና ተከታዮች ዘንድ ዛሬ ተከብሮ ይውላል::

ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም