ቀጥታ፡

አቶ ርስቱ ይርዳው በብላቴ የኮማንዶና አየር ወለድ ሃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እያካሄዱ ነው

ብላቴ ሰኔ 30/2014(ኢዜአ)…በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳውና የክልሉ አመራሮች በብላቴ የኮማንዶና አየር ወለድ ሃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እያካሄዱ ነው።

በሥነሥርዓቱ ላይ የማዕከሉ አዛዦች፣ አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞችና  የፌዴራል ፖሊስ አባላት እየተሳተፉ ነው።

በደቡብ ክልል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ከ1 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የሚተከሉበት የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ሰኔ 27/2014  መጀመሩ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም