የኢትዮጵያ እና ሱዳን ህዝቦች በርካታ አንድ የሚያደርጓቸው ጉዳዮች አሉ፤ ችግሮቻቸውንም በጋራ ለመፍታት ይሰራሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እና ሱዳን ህዝቦች በርካታ አንድ የሚያደርጓቸው ጉዳዮች አሉ፤ ችግሮቻቸውንም በጋራ ለመፍታት ይሰራሉ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ሰኔ 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ እና ሱዳን ህዝቦች በርካታ አንድ የሚያደርጓቸው ጉዳዮች አሉ፤ ችግሮቻቸውንም በሰላም ለመፍታት በጋራ ይሰራሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከኢጋድ ጉባኤ ጎን ለጎን ከሱዳን ሪፐብሊክ የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብደል ፈታሕ አል ቡርሃን ጋር ተወያይተዋል።
ሁለቱ መሪዎች በወቅታዊ ቀጣናዊ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ነው የተወያዩት።
አገራቱ ከድንበር ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ያጋጠሟቸውን ችግሮች በውይይት በሚፈቱበት ጉዳይ ላይም ምክክር አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሁለቱ አገሮች ችግሮቻቸውን በውይይት በመፍታት ግንኙነታቸውን ይበልጥ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ እና ሱዳን ህዝቦች በርካታ አንድ የሚያደርጓቸው ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ ሁለቱ ህዝቦች ችግሮቻቸውን በሰላም ለመፍታት በጋራ ይሰራሉ ብለዋል።
የረጅም ዘመን የተሳሰረ ታሪክ ያላቸውን የሁለቱን አገራት ህዝቦች በጋራ ልማት ተጠቃሚ ማድረግ ላይ ያተኮረ ስራ መስራት እንደሚገባም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ39ኛው የኢጋድ መሪዎች አስቸኳይ ጉባኤ ለመሳተፍ ዛሬ ማለዳ ኬንያ ናይሮቢ መግባታቸው ይታወቃል።