የበድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ማህበር አባላት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የበድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ማህበር አባላት አዲስ አበባ ገቡ
ሰኔ 27 ቀን 2014 (ኢዜአ) ተቀማጭነቱ ዋሽንግተን ዲሲ የሆነው በድር የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሙስሊሞች ማህበር አባላት አዲስ አበባ ገቡ።
አባላቱ አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱኳን አያኖና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሀመድ እድሪስን ጨምሮ የተለያዩ አካላት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የበድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ማህበር አባላት አዲስ አበባ መግባት ከኢድ እስከ ኢድ መርሃ ግብር አካል መሆኑም ታውቋል።
በድር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሙስሊሞች ማህበር 22ኛ ኮንፈረንሱን በመጪው ሀምሌ ወር “በድር ወደ ማንነት” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ መግለጹ ይታወሳል።
የማህበሩ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በኢትዮጵያ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ በመሰማራት ለአገር ዕድገት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ በማገዝ ረገድም ኮንፍረንሱ ዕድል ይሰጣል።
በድር ኮንፈረንስ ኢትዮጵያን የማያውቁ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን በመጎብኘት ስለአገራቸው ታሪክ እንዲያውቁ በማድረግ በኩልም ፋይዳው የጎላ ነው።