ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክትን መርቀው ከፈቱ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክትን መርቀው ከፈቱ

ሰኔ 26 ቀን 2014 (ኢዜአ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የለገዳዲ ምዕራፍ ሁለት የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክትን መርቀው ከፍተዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በመደበው 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በጀት የተሰራና በቀን 86 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችል ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የውሃ ማምረቻው እያንዳንዳቸው ከ2 ሺ እስከ 5 ሺ ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያላቸው 16 ጥልቅ ጉድጓዶች አሉት፡፡
በተጨማሪም 10 የውሃ ማጠራቀሚያ ጋን ግንባታን የያዘ ነው።
ፕሮጀክቱ የ12 ኪሎ ሜትር ዋና የውሃ መስመር፣72 ኪሎ ሜትር የውሃ ማሰባሰቢያ መስመር፣ 99 ኪሎ ሜትር የስርጭት መስመር ዝርጋታ አካቷል፡፡
ሁለት ግዙፍ የግፊት መስጫ ጣቢያዎች እና 38 ኪሎ ሜትር የመዳረሻ መንገድን፣ እንዲሁም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች እና በጉድጓዶቹ አካባቢ የሚሰሩ የሲቪል ስራዎችን አኳቷል።
ይህ ፕሮጀክት የከተማ አስተዳደሩን በቀን ውሃ የማምረት አቅሙን ከ674 ሺህ ወደ 760ሺህ እንደሚያሳድገው ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ