አምባሳደር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት አቀረቡ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት አቀረቡ

ሰኔ 25 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አቅርበዋል።
በተጨማሪም አምባሳደሩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ብሊንከንና ባለቤታቸው ባዘጋጁት መርሃ ግብር ላይ መሳተፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ የኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነት አስመልክቶ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጿል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤