ቀጥታ፡

የሰላምና የልማት ፎረም እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የችግኝ ተከላ አካሄዱ

ሰኔ 25/2014 /ኢዜአ/ በባለሀብቶችና የሥራ ፈጣሪዎች ትብብር የተመሠረተው የሰላምና የልማት ፎረም እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ አካሄዱ

የፎረሙ የበላይ ጠባቂዎች የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲሁም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያና የኮሚሽኑ ሠራተኞች ተገኝተዋል።

የችግኝ ተከላው "ኑ ሰላምን እንትከል ኑ እርቅን እንትከል ኑ እድገትን እንትከል ኑ እህትማማችነትን ወንድማማችነትን እንትከል ኑ እንወያይ" በሚል መሪ መልዕክት ነው የተካሄደው።

የሰላምና የልማት ፎረሙ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በዚህ ወቅት እንዳሉት ለሀገራችን ሰላምና የአረንጓዴ ልማት በእጅጉ ያስፈልጋታል።

በመሆኑም ኢትዮጵያውያን ለሰላም ሊሰሩ ይገባል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም