ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በፈረንሳይ በተካሄደ የንግድ ኤግዚቢሽን የቆዳ ውጤቶችን አስተዋወቀች

አዲስ አበባ መስከረም 2/2011 ኢትዮጵያ በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የቆዳ ውጤቶችን አስተዋወቀች። በኤግዚቢሽኑ በአገሪቱ የቆዳ ዘርፍ የተሰማሩ የተለያዩ ኩባንያዎች ቦርሳ፣ ጫማና አልባሳትን በመያዝ ተሳትፈዋል። በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር አሊ ሱሌይማን ''ኢትዮጵያን ሃይላንድ ሌዘር'' የተባለው ብራንድ በአውሮፓ ህብረት እንዲመዘገብ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ምርቶቹ በኤግዚቢሽኑ እንዲተዋወቁ የጃፓኑ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጄንሲ ስፖንሰር ማድረጉም ታውቋል። ኢትዮጵያ እንደ ኢጣልያ፣ ቻይና፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ሩሲያ እና ሆንግ ኮንግ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልከው የቆዳ ምርቶች 75 በመቶ የሚሆነው ምርት መዳረሻዎች ናቸው። የኢትዮጵያ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ከአቅርቦት፣ ከጥራት፣ ከገበያ፣ ከሰለጠነ የሰው ኃይልና ከገንዘብ አቅርቦት ጋር የተያያዘ ድክመቶች እንዳሉበት ይነገራል። የቆዳና ሌጦ አቅርቦት ሰንሰለትም ቅንጅት የጎደለው ነው። የዘርፉ ተዋንያኖች የእሴት ሰንሰለቱን ተከትለው የሚያደርጉት እንቅስቃሴም በተናጥል በመሆኑ መደጋገፍና አብሮ መስራት አይታይበትም።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም