ቀጥታ፡

የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ለቱሪዝም ዘርፍ እድገት ያለው አስተዋጽኦ የተመለከተ ውይይት በሰመራ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 23 ቀን 2014 (ኢዜአ)የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ለቱሪዝም ዘርፍ እድገት ያለው ሚና የተመለከተ ውይይት በሰመራ በመካሄድ ላይ ነው።

በውጭ ግንኙነት ኢንስቲትዩት አማካኝነት የተዘጋጀ ውይይት ለአንድ ቀን የሚቆይ ሲሆን የተለያዩ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበዉ ምክክር ይደረግባቸዋል ተብሏል።

ጽሁፎቹ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ስትራቴጂያዊ ቅኝት ለቱሪዝም ዘርፉ እድገት፣ብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ የመገንባት ትልም እንዲሁም የኢትዮጵያ ቱሪዝም ዲፕሎማሲ ስትራቴጂ አቅጣጫዎች፣ ትግበራና ተግዳሮት የሚሉ ጉዳዮች እንደሚዳስስ ተነግሯል።

በውይይቱ ላይ የፌደራልና የክልል ተቋማት አመራሮች፣የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተወካዮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም