በመዲናዋ በበጀት ዓመቱ 161 ሺህ ስራ አጦች የስራ እድል ይፈጠርላቸዋል ተባለ

አዲስ አበባ መስከረም 2/2011 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2011 ዓ.ም ከ161 ሺህ በላይ ስራ አጦች ስራ እንደሚፈጠርላቸው የከተማዋ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራዝ ልማት ቢሮ ገለጸ።  ለዚህም ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ከአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም እንዲሁም ከወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ መዘጋጀቱ ተገልጸዋል።  የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሚኪያስ ሙሉጌታ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት የስራ ዕድሉ ከሚፈጠርላቸው ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ ወጣቶች ሲሆኑ ከ50 በመቶ በላይ ደግሞ ሴቶች ይሆናሉ።  ከወትሮው በተለየ በ2011 ወጣቶችንና ሴቶችን በስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ ለማድርግ በትኩረት እየተሰራ ነውም ብለዋል።  የመስሪያ ቦታ የማዘጋጀት፣ብድር የመፈለግና የተዘዋዋሪ ፈንዱን እና ሌሎች አስፈላጊ ስራዎችን የማመቻቸት ስራዎች እየተሰሩ እነደሆነም ገልጸዋል። የስራ ዕድል የሚፈጠርባቸው መስኮች በአምስት ዋና ዋና ዘርፎች እንደሚከፈል የገለጹት አቶ ሚኪያስ በማኑፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን ዘርፍ፣ የከተማ ግብርና፣ የአገልግሎትና የንግድ ዘርፎች ናቸው ብሏል። በዘርፉ የሚታየውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለማስቀረትም የአንድ መስኮት አገልግሎት የመስጠት ስራ ተጀምሯል ብለዋል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም