የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ከግልገል በለስ እስከ አባይ ግድብ የሚደርሠውን የመንገድ ስራ አጠናቆ አስመረቀ

141

ሰኔ 21 2014 (ኢዜአ) ዋና መምሪያው 210 ኪ.ሜ ርዝማኔ ያለውን 3ኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ ወደ ከፍተኛ ደረጃ የጠጠር መንገድ በማሳደግ በተቀመጠለት የግዜ ሠሌዳ አጠናቆ ማስመረቁ ተገልጿል።

መንገዱን መርቀው የከፈቱት የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል ደስታ አብቼ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ በላቸው ካሳ ናቸው።

ሌተናል ጀኔራል ደስታ አብቼ በዕለቱ ባደረጉት ንግግር የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የግልገል በለስ-አባይ ግድብ የመንገድ ፕሮጀክትን ስራ ሲረከብ የተሠጠው የመንገድ ፕሮጀክት ስራ ብቻ ሳይሆን ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነትና አደራም ነበር ብለዋል።

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውሉ ግብዓቶች ሲጓጓዙ በመንገድ ላይ እስከ ሁለት ሳምንት ይቆዩ እንደነበር አስታውሰው የመሃንዲስ ክፍሉ ባከናወነው መንገድ የማሻሻል ጥገና ስራ የግድቡ የግንባታ ግብዓቶች በአንድ ቀን ለመድረስ ይችላሉ ብለዋል።

ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው በምረቃ ስነ ስረዓቱ ላይ የአካባቢው መስተዳደር አካላት፣ የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም