በ272 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የነጆ ኢፈ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተጠናቆ ስራ ጀመረ

52

ግምቢ ሰኔ 21/2014 /ኢዜአ/ በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ በ272 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የኢፈ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል።

ትምህርት ቤቱ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉና የዞኑ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቆ ስራ ጀምሯል።

የክልሉ መንግስት በኢፈ ቦሩ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት አቅዶ እየገነባቸው ያሉ ትምህርት ቤቶች አካል የሆነው የነጆ አዳሪ ትምህርት ቤት 272 ሚሊየን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል።

የነጆ ኢፈ ቦሩ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ነሐሴ 2012  ዓ.ም ተጀምሮ በአጭር ጊዜ የተጠናቀቀ መሆኑም ተናግረዋል።

የትምህርት ቤቱ በአካባቢው መገንባት ለወላጆችና ለተማሪዎች እፎይታን የሰጠ መሆኑንም አስተያየታቸውን የሰጡ ወላጆች ተናግረዋል።

አመራሮቹ ከትምህርት ቤቱ ምረቃ በኋላ በትምርት ቤቱ ግቢ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አካል የሆነውን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

በምረቃው ስነ ስርዓት የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳና ምክትል ፕሬዝዳንት አወሉ አብዲ፣ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሠማ፣ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር  ቶላ በሪሶ እንዲሁም የክልሉ፣ የዞኑና የወረዳው የስራ ሃላፊዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም