"ኢትዮጵያ ከነባር ችግሮቿ ተላቅቃ በተስፋዋ ጎዳና እንድትገሠግሥ እየታገልን ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

84

ሰኔ 19 ቀን 2014 (ኢዜአ)“ኢትዮጵያ ከነባር ችግሮቿ ተላቅቃ በተስፋዋ ጎዳና እንድትገሠግሥ እየታገልን ነው ያለፈው ችግሯ ውርስ መከራችንን ሊያረዝመው ይታገለናል። እኛ ደግሞ ተስፋችንን ለማለምለም እንታገላለን።በችግራችን ከተዋጥን ይነግሥብናል። ለተስፋችን ከታገልን እንነግሥበታለን”ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ::

"በዚህ እሑድ ሁላችንም መቻቻልና አብሮነት እንዲያሸንፍ እንጸልይ።ነጋችን ብሩህ እንዲሆን ደግሞ ወጥተን ዛፎችን እንትከል።ተሸናፊው ውርስ ችግር ሊያሳምመን እንጂ ሊያሸንፈን አይችልም" ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት::

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም