ለታላቋ ኢትዮጵያ ታላቅ አየር ኃይል መገንባት ያስፈልጋል- ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

138

ሰኔ 18 ቀን 2014 (ኢዜአ) ለታላቋ ኢትዮጵያ ታላቅ አየር ኃይል መገንባት ያስፈልገናል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የተዋጊ አውሮፕላንን እንዲሁም በተለያዩ አውሮፕላን አብራሪነት የሰለጠኑ አባላቱን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አስመርቋል።

ፕሬዝዳንቷ በዚህ ወቅት "ከልጅነት እስከ እውቀት ኩራት የሚሰማኝ የአገሩን ዳር ድንበር ለመጠበቅ ውድ ሕይወት ለሚከፍለው አገር አገር የሚሸት የአገር መከላከያ ሰራዊቱ መካከል ስገኝ ነው" ብለዋል።

አየር ኃይሉ ባለፉት 90 ዓመታት አኩሪ ገድል ፈፅሟል፣ ለአገር ሉዓላዊነት መስዕዋትነት ከፍሏል ሲሉ አውስተው አየር ኃይሉ በየጊዜው የሚመጥን አቅም መያዝ እንዳላበት ገልጸዋል።

የተቋማት ሪፎርም ውጤቱንም በአየር ኀያሉ ትርዒቶች መመልከታቸውን ጠቅሰዋል። አየር ኃይሉ የተራቀቀ ትጥቅና ዘመናዊ ትክኖሎጂ ማሟላት አስፈላጊ መሆኑንና ለዚህም በቂና ብቁ የሰው ኃይል መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የአየር ኃይሉን መምሪያ የፈጠረው ምቹ አካባቢ ስራ አስገራሚ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ይህም ምርታማ የሰው ኃይል ለማፍራት ያግዛል ብለዋል።

ቀጣይነት ያለው ብቁና በቂ የሰው ኃይል ማፍራት እንደሚገባና ከአብራሪዎቹ በተጨማሪ በአጠቃላይ የአየር ኀያል ባለሙያዎች እና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ማብቃት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የመከላከያ እና የደህንነት ተቋማት ሪፎርም ማጠናከርና ለተልዕኮ ብቁ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ መንግስታዊ ስርዓት ቢለወጥ የማይለዋወጥ አገር የሚጠብቅ በመሆኑ እኛም አገርን ለትውልድ ማሻገር እንዳለበት ገልፀዋል።

የሰው ልጅ በሕይወት የመኖር መብት መጠበቅ እንደሚገባ፣ አገርን ከሁላችንም ከቃላት በላይ አገርን በተግባር መጠበቅ አለብን ብለዋል።

ለታላቁ አገር ታላቅ ታላቅ አየር ኃይል መገንባት ያስፈልገናል ብለዋል ፕሬዚዳንቷ።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም