በሚወጡ መመሪያዎች ዙሪያ የዜጎችን ተሳትፎ ማሳደግና የመብት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል- ፍትህ ሚኒስቴር

223

ሰኔ 18 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአገሪቷ በሚወጡ መመሪያዎች ዙሪያ የዜጎችን ተሳትፎ ማሳደግና የመብት ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ ፈቃዱ ጸጋ ገለጹ።

የፍትህ ሚኒስቴር የአስተዳደር  ስነ-ስርዓት አዋጅ አፈፃጸም ክትትል ሪፖርት ከተደረገባቸው የገንዘብ ሚኒስቴር፣ ጤና ሚኒስቴር፣ ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

በቢሾፋቱ ከተማ እያካሄደ በሚገኘው ውይይት ላይ የየተቋማቱ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ዓ.ም ምንነት እና የገንዘብ ሚኒስቴር አፈፃጸም ሪፖርት ለውይይት መነሻነት ቀርበዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ ፈቃዱ ጸጋ፤ ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት ተቋማዊና መዋቅራዊ ለውጥ ላይ መሆኗን ጠቅሰው የዜጎችን መብት ለማስጠበቅ አዋጅና መመሪያ ወጥቶ ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

የሚወጡ መመሪያዎችም የዜጎችን ተሳትፎ በማሳደግ በመብታቸው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

መንግስት ህግን በማውጣት ለዜጎች ሁለንተናዊ መብት መከበር በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም