ብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት በአምስት ዘርፎች ተዘጋጅተው የቀረቡለትን 400 ብሔራዊ ደረጃዎች አጸደቀ

179

ሰኔ 17 ቀን 2014(ኢዜአ) ብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት በአምስት ዘርፎች ተዘጋጅተው የቀረቡለትን 400 ብሔራዊ ደረጃዎች አጸደቀ።

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ምክር ቤቱ ያጸደቃቸውን ብሔራዊ ደረጃዎች በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የጸደቁ ደረጃዎች በኮንስትራክሽን ሲቪል ኢንጅነሪንግ፣ በአካባቢና ጤና ደህንነት፣ በኤሌክትሮ መካኒካል የደረጃ ዝግጅት፣ በግብርናና ምግብ የደረጃ ዝግጅት እና በኬሚካልና ኬሚካል ውጤቶች ዘርፍ ነው፡፡

ከእነዚህ መካከል 69 አዲስ፣ 125 የተከለሱ፣ 206 በማስቀጠል እና ከህዝብ ጤና እና ደህንነት ጋር የተገናኙ እንዲሁም ዘጠኙ በአስገዳጅነት የፀደቁ ደረጃዎች መሆናቸው ተጠቁሟል።

የፀደቁት የኢትዮጵያ ደረጃዎች ከሀገራዊ የልማት ስትራቴጂ ጋር የተቃኙ መሆናቸውም ተጠቅሷል።

የፀደቁት 400 ብሄራዊ ደረጃዎች የብሔራዊ ደረጃዎች ምክር ቤት ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 33ኛው የምክር ቤት ስብሰባ እና ሰኔ 03 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ስብሰባ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም