የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሪዎች ዛላምበሳ ገቡ

መቀሌ መስከረም  1/2011 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ዛላምበሳ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች  በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ከ20 ዓመታት በኋላ በተጀመረው  የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ ለመገኘት ነው ወደስፍራው ያመሩት፡፡ ከዛላምበሳ ከተማ አልፍ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ እና  ኤርትራ  ድንበር አካባቢ የሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት  ወደ ነበረበት  ለመመለስ በተዘጋጀ መድረክ ለመገኘት መሪዎቹ በስፍራው ሲደርሱ የሁለቱ ሀገራት መከላከያ ሰራዊት አባላት በሁለት ረድፍ በመሆን አቀባባል አድርገውላቸዋል፡፡ የሁለቱም ሀገራት ሰንደቅ ዓላማ በስፍራው እየተውለበለበ ይገኛል፡፡ በመድረኩ ከሁለቱ ሀገራት የተወጣጡ ህዝቦች እንዲሁም የኤርትራና የኢትዮጵያ ከፍተኛ መኮንኖችና ባለሰልጣናት ተገኝተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እና ኤርትራን የሚያገናኘው የመቀሌ ዛላንበሳ ሰንአፈ አስመራ መንገድ ዛሬ እንደሚከፈት ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም