በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ - ኢዜአ አማርኛ
በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ
ኒውዮርክ መስከረም 1/2011 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አምዴ ትናንት የሹመት ደብዳቤያቸውን ለድርጅቱ አቀረቡ። የአምባሳደር ታዬን የሹመት ደብዳቤ የተቀበሉት የድርጅቱ ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ናቸው። አምባሳደር ታዬ የተመድ ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ከመሾማቸው በፊት በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል። ከዚህም ሌላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥም ሚኒስትር ዴኤታን ጨምሮ በሌሎች ከፍተኛ ኃላፊነቶች ሰርተዋል። በአሜሪካ ዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አማካሪ እና በሎስአንጀለስ የኢትዮጵያ ዋና ቆንስላ በመሆንም ለረጅም ዓመታት በኃላፊነት አገልግለዋል። አምባሳደር ታዬ የመጀመሪያ ዲግሪ በፖለቲካ ሳይንስና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያገኙ ሲሆን ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከእንግሊዝ ላንካስተር ዩኒቨርሲቲ በዓለምቀፍ ግንኙነትና ስትራቲጂያዊ ጥናት አግኝተዋል።