ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጀመረ

መቀሌ መስከረም 1/2011 በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ከ20 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ  የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጀመረ፡፡ በአዲሱ ዓመት በመባቻ ላይ ላይ ከዛላንምበሳ ከተማ አለፍ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤርትራ  ድንበር አካባቢ የሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት ወደ ነበረበት  ለመመለስ መድረክ ተዘጋጅቷል በመድረኩ ከሁለቱ ሀገራት የተወጣጡ ህዝቦች እንዲሁም በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና እና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተገኝተዋል፡፡ ኢትዮጵያእና ኤርትራን የሚያገናኘው የመቀሌ ዛላንበሳ ሰንአፈ አስመራ መንገድ ዛሬ እንደሚከፈት ይጠበቃል፡፡ በዚሁ መድረክ የኤርትራው ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይገኛሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም