በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስ እና ሕጋዊነት ኦዲት ወቅት ከታዩ ዋና ግኝቶች ለምክር ቤቱ ቀረቡ

85

ሰኔ 14/2014 /ኢዜአ/ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የ2013 በጀት ዓመት በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስ እና ሕጋዊነት ኦዲት ወቅት የታዩ ዋና ግኝቶች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረበ፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የ2013 በጀት ዓመት የኦዲት ክዋኔ ሪፖርትን ለምክር ቤቱ እያቀረበ ይገኛል፡፡

በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስ እና ሕጋዊነት ኦዲት ወቅት ከታዩ ዋና ግኝቶች፤ የጥሬ ገንዘብ ሒሳብ አያያዝ እና አጠባበቅን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ኦዲት መደረጉ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ አንስተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ብር 1,491,901.91 እና ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ብር 21,749.54 በድምሩ ብር 1,513,651.45 የጥሬ ገንዘብ ጉድለት መገኘቱ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በ3 መሥሪያ ቤቶች በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ብር 632,044.97፣ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ብር 241,244.00 እና በቀብሪዴሃር ዩኒቨርስቲ ብር 128,030.00 በድምሩ ብር 1,001,318.97 በክፍያ መመሪያ ከተወሰነው የገንዘብ መጠን በላይ በጥሬ ገንዘብ ወይም በቼክ ወጪ የተደረገ ሒሳብ መገኘቱ በቀረበው ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡

በሌላም በኩል በወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለረጅም ዓመታት ሒሳብ ሳይደረግ በባንክ ውስጥ የተጠራቀመ የገቢ ሒሳብ ብር 87,909,298.90 ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም