ኢትዮጵያ አራተኛውን ዙር አረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ዛሬ በይፋ ትጀምራለች

674

ሰኔ 14/202014 /ኢዜአ/ ኢትዮጵያ አራተኛውን ዙር አረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ዛሬ በይፋ ትጀምራለች።

በ2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያስጀመሩት አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዘንድሮም ለአራተኛ ዙር ይቀጥላል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሻራቸውን በማኖር መርሐ ግብሩን በይፋ እንደሚያስጀምሩ ይጠበቃል።

ባለፉት ሶስት ዙሮች በመጀመሪያው 4 ቢሊዮን፣ በሁለተኛው 5 ቢሊዮን፣ በሶስተኛው 6 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 18 ቢሊዮን ችግኞች  ተተክለዋል።

በ4 ተከታታይ ዓመታት ውስጥ 20 ቢሊየን ችግኞች ለመትከል ውጥን በተያዘው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በዘንድሮው ክረምት 6 ቢሊየን ችግኞች ለመትከል ታቅዷል።

አራተኛ ዓመቱን የያዘው አረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያላትን ቁርጠኝነት ለዓለም ያሳየ ነው።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ደን የማልማት ዘመቻው ከኢትዮጵያ አልፎ ለጎረቤት አገራትም ችግኝ ተደራሽ ያደረገና ለችግኝ ተከላ ያነሳሳ መርሐግብር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም