ቀጥታ፡

ዶክተር አብይ በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር ቡሬ ግንባር አዲስ ዓመትን እያከበሩ ነው

አዲስ አበባ መስከረም 1/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያና በኤርትራ ድንበር ቡሬ ግንባር በመገኘት ከሁለቱ አገሮች መከላከያ ሰራዊቶች ጋር አዲስ አመትን እያሳለፉ እንደሚገኙ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ጽህፈት ቤት ገልጿል። የሁለቱ አገሮች መሪዎች አዲስ ዓመትን የሁለቱ አገሮች መከላከያ ሰራዊቶች በአንድነት ሆነው በአገሮቹ መካከል ያለውን የሰላም ግንኙነት በሚያጠናክር መልኩ በዓሉን እያከበሩ ይገኛል። በሁለቱ አገሮች መካከል የተፈጠረውን እርቅ ተከትሎ ለአመታት ተፈጥሮ የነበረውን መራራቅና መገፋፋት ለማስቀረት የሚያስችሉ ሁለንተናዊ የወዳጅነት ግንኙነት ጀምረዋል። በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት የተነሳ ስራ አቁመው የነበሩ የኢትዮጵያ መርከቦች ከ20 አመታት በኋላ  ስራ ለመጀመር የመጀመሪያ የሆነችውን የ'መቀሌ' መርክብ በምጽዋ ወደብ ነሐሴ 30 ቀን 2010 መልህቋን ስትጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስፍራው መገኘታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ የተጀመረው የሰላምና የመግባባት ሂደት ውጤት እያሳየ ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም