የመጀመሪያው የቻይና እና የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

159

ሰኔ 13 ቀን 2014 (ኢዜአ)የመጀመሪያው የቻይና እና የአፍሪካ ቀንድ(China-Horn Africa) የሰላም ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ጉባዔው በአፍሪካ ቀንድ አገራት ሰላም፣ መልካም አስተዳደርና የልማት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።

ኮንፈረሱ የሚካሄደው ባሳለፍነው ወርኃ የካቲት ቻይና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ሹ ቢንግ ከሾመች በኋላ ሲሆን ጉባዔው የቀንዱ አገራት አንድነት እንዲጠናከር፣ለረጅም ጊዜያት ግጭትና ብጥብጥ ባልተለየው ቀጣና ሠላምና ልማት እንዲረጋገጥ ቻይና ከአገራቱ ጋር በጋራ ለመስራት ያላትን ፍላጎት ታላሚ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የአፍሪካ ቀንድ አገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬኒያ፣ሶማሊያ፣ጅቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኡጋንዳ፣ሱዳንና ደቡብ ሱዳንን በአጠቃላይ 8 አገራትን ያጠቃለለ የምስራቅ አፍሪቃ ቀጣና ነው።

ቻይና በቀጣናው መጠነ ሰፊ ኢንቨስትመንት ያፈሰሰች ሲሆን አፍሪካን ከመካከለኛው ምስራቅ የሚያስተሳስረው የቤልትና ሮድ ፕሮጀክትም ግዙፉ ተጠቃሽ ነው።

በጉባዔው የቀንዱ አገራት እና የቻይና መንግስት ልዑካን ታድመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም