ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ወደአገራቸው የተመለሱ ታዋቂ የኢትዮጵያ የፖለቲካና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን አደነቁ

አዲስ አበባ ጳጉሜ 5/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ የቀረበላቸውን ጥሪ አክብረው ወደአገራቸው የመጡ ታዋቂ የኢትዮጵያ የፖለቲካና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን አደነቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አድናቆታቸውን የገለፁት 'በፍቅር እንደመር፣ በይቅርታ እንሻገር' በሚል ዛሬ ምሽት እየተካሄደ ባለው የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ መርሃ-ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ላለፉት 40 ዓመታት በመሰላቸው መንገድ ሲታገሉ ቆይተው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስታቸውን እምነት ዛሬ እዚህ መድረክ ላይ የተገኙትን ታዋቂ የፖለቲካና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ኢትዮጵያዊያንን አመስግነዋል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን፣ ዶክተር አረጋዊ በርሄን፣ ዶክተር ዲማ ነገኦ፣ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ አርቲስት ታማኝ በየነን፣ አርቲስትና ገጣሚ አለምጸሐይ ወዳጆ፣ አቶ ጃዋር መሀመድንና ሌሎችም  በስም የጠቀሷቸው ወደአገር ቤት በመመለሳቸው አድናቆታቸውን ገልፀዋል። እነዚህ አንጋፋ የኢትዮጵያ ልጆች ከሌሎች ወገኖቻቸው ጋር በመደመር ለአገር ሰላምና አድገት በጋራ እንዲሰሩም ጥሪ አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም