"ስለ ኢትዮጵያ" የፎቶግራፍ አውደ ርዕይና ፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

44

ሰኔ 9 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው አራተኛው "ስለኢትዮጵያ" የተሰኘው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕዩ በኢትዮጵያ ከ1950ዎቹ አንስቶ በየዘመኑ የተከሰቱ ወሳኝ ፖለቲካዊና ማህበራዊ የታሪክ አንጓ ያላቸው ሁነቶችን የሚያሳይ ነው ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናኒሴ ጫሊን ጨምሮ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራልና የክልሎች የሥራ ኃላፊዎች ታድመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ቀደም ሲል በጅግጅጋ፣ ድሬደዋና ሐረር ከተሞች ተመሳሳይ መድረኮችን ማዘጋጀቱ የሚታወስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም