ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ውስጥ አምስት ጉዳዮች ሚዛን መጠበቅ እንዳለባቸው አስገነዘቡ

133

ሰኔ 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ውስጥ አምስት ጉዳዮች ሚዛን መጠበቅ እንዳለባቸው አስገነዘቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያዌዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የአምስት ጉዳዮችን ሚዛን ጠብቆ መጓዝ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ዴሞክራሲና ሰላም፣ የብሔር ጉዳይና የአገር ጉዳይ፣ የግለሰቦችና የቡድን መብት፣ የትናንት ታሪክና የትናንት ፈተና እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምና የዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ሚዛናቸውን ጠብቀው መሄድ የሚኖርባቸው አምስት ጉዳዮች መሆናቸውን አንስተዋል።

ዴሞክራሲና ሰላም ሚዛናቸውን ጠብቀው እንዲሄዱ መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ አንዱ ሌላኛውን እንዳይውጥ ሚዛን መጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

የብሔርና የአገር ጉዳይን ሚዛንን ማስጠበቅ በሚመለከት እንደተናገሩት ሁለቱን አስጠብቆ ለማስቀጠል አማካኝ እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።

የግለሰብና የቡድን መብትን በተመለከተ ሚዛንን መጠበቅ አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ በግል ወንጀል ከሰሩ በኋላ የቡድን ስም መያዝ እንደማይገባ ገልጸዋል።

የትናንት ታሪክንና የትናንት ፈተናን ሚዛን ማስጠበቅ እንደሚገባ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የብሔራዊ ጥቅምና የዓለም ዓቀፍ ግንኙነትን ሚዛን ማስጠበቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም