የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል

99

ሰኔ 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በተያዘው አጀንዳ መሠረትም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ጥያቄዎችን እያቀረቡ ነው።

በምክር ቤቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዓለም-አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የኃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም