ተመድ እየተባባሰ የመጣውን የዓለም ሰብአዊ ቀውስ ለማስቆም መንግስታት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጠየቀ

116

ሰኔ 06 ቀን 2014 (ኢዜአ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በአለም አቀፍ ደረጃ እየተባባሰ የመጣውን ሰብአዊ ቀውስ ለማስቆም መንግስታት አስቸኳይ የመፍትሔ እርምጃ እንዲወስዱ ጠየቀ።

በተመድ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሃላፊ ሚሼል ባችሌት 50ኛውን የሰብአዊ መብቶች አለም አቀፍ ጉባኤ በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት በአለም 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ገደማ ሰዎች በምግብ፣ በሃይልና በፋይናንስ እጥረት ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

May be an image of 1 person and text that says "UNITED NATIONS HUMAN RIGHTS COUNCIL 50th SESSION Day 1 13 June 2022 SAJQUE Oo"

በኮቪድ-19 ወረርሽኝና በግጭቶች የተነሳ በምግብ አቅርቦት የተቸገሩ ሰዎች ቁጥር ከ320 ሚሊዮን በላይ ሊሆን እንደሚችል ገልጸው፤ የሰብአዊ ቀውስ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ፍትሐዊ ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ለዚህም እጅግ አስቸኳይና ተራማጅ የመፍትሄ እርምጃ ከመንግስታት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።

ሰብአዊ ቀውሶችን በመከላከል ረገድ የማይተካ ሚና ያላቸው አለም አቀፍ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማትም የችግሩን አሳሳቢነት ተረድተው ሊሰሩ እንደሚገባ አመልክተዋል።

ችግሩ በስፋት በሚታይባቸው ሀገራት የሰብአዊ ቀውስን ለመፍታት የሚያስችል ፕሮጀክት በተመድ መነደፉን ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ወቅት 4 ቢሊዮን ሰዎች ከአደጋ የሚጠበቁበት የተሟላ ከለላ እንደሌላቸው ከተመድ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም