አትሌት ማሞ ና አትሌት ዝናሽ 38ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር አሸነፉ

186

ሰኔ 5 ቀን 2014 (ኢዜአ)አትሌት ማሞ መንግስቱና አትሌት ዝናሽ ጋረደው በባህር ዳር ከተማ የተካሄደውን 38ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር አሸነፉ፡፡

በውድድሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ማሞ መንግስቱ ከኦሮሚያ ፖሊስ በአንደኝነት አጠናቋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አትሌቶች የሆኑት ፅዳት አበጀና አሰፋ ተፈራ እንደየቅደም ተከተላቸው ውድድሩን በሁለተኛ እና ሶስተኝነት አጠናቀዋል፡፡

በሴቶች ምድብ ደግሞ አትሌት ዝናሽ ጋረደው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ በአንደኝነት አጠናቃለች።

አያንቱ ገመቹ ከፌደራል ፖሊስ ሁለተኛ ሆና ስትጨርስ፤አትሌት ብዙአገር አደራ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሶስተኛ ወጥታለች።

በውድድሩ በሁለቱም ፆታዎች አንደኛ ሆነው ላጠናቀቁ አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ሁለተኛ ለወጡት አትሌቶች ለእያንዳንዳቸው 25 ሺህ ብር፤ በሶስተኛ ሆነው ላጠናቀቁት ደግሞ 20 ሺህ ብር ሽልማት ተሰጧቸዋል።

በውድድሩ እስከ ስምንተኛ ለወጡ አትሌቶች እንደየደረጃቸው የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በውድድሩ 135 የወንድና 101 የሴት አትሌቶች የተካፈሉ ሲሆን፤ የአንጋፋ አትሌቶች ውድድርም ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም