ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊያና በጅቡቲ ያደረጉትን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሊያና በጅቡቲ ያደረጉትን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

ሰኔ 4 ቀን 2014 (ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሶማሊያና በጅቡቲ ያደረጉትን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ በዓለ-ሲመት ላይ በመገኘት መልዕክት ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው።

ከሶማሊያ ጉብኝታቸው በኋላ ወደ ጅቡቲ በማቅናት ከአገሪቷ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ጋር በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል።