ህፃናትን፣ወጣቶችን፣አረጋውያንና አካል ጉዳተኞችን ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ህፃናትን፣ወጣቶችን፣አረጋውያንና አካል ጉዳተኞችን ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው

ሀዋሳ ሰኔ 4/2014 (ኢዜአ) ህፃናትን ወጣቶችን አረጋውያንና አካል ጉዳተኞችን በሁሉም መስኮች ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
ሚኒስቴሩ በተሰጠው ሃላፊነትና ተግባራት ዙሪያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ያዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና በሀዋሳ ከተማ እየተሰጠ ነው።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለጹት ሴቶችን ህፃናትን ወጣቶችን አረጋውያንና አካል ጉዳተኞችን በሁሉም መስኮች ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

ሚኒስቴሩ ከተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት በመነሳት ሴቶችን ህፃናትን ወጣቶችን አረጋውያንና አካል ጉዳተኞችን በሁሉም መስኮች ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ አየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ተቋሙ በሚያስፈፅማቸው ፖሊስዎች ስትራቴጂዎችና አለም አቀፍ የስምምነት ሰነዶችን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑን አመላክተዋል።
ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ላይ የህዝብ ተወካዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላትን ጨምሮ ከክልልና ከከተማ አስተዳደሮች ቢሮዎች የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።