የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያስገነባው የረገ ኤያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያስገነባው የረገ ኤያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ
187
ሰኔ 04 ቀን 2014 (ኢዜአ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ያስገነባው የረገ ኤያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
ትምህርት ቤቱ በውስጡ 10 መማሪያ ክፍሎች ፣ ቤተ -ሙከራ፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ የተማሪ ክሊኒክ ፣የአስተዳደር ሕንጻና የስብሰባ አዳራሽ ያካተተ ነው ።
በወረዳው ማመዴ ቀበሌ የተገነባው ይህ ትምህርት ቤት በክልሉ በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ተገንብቶ ለምረቃ የበቃ ሁለተኛው ትምህርት ቤት መሆኑ ተመላክቷል ።