“ኢትዮ- ሰላም ሩጫ በወላይታ” የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
“ኢትዮ- ሰላም ሩጫ በወላይታ” የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 04 ቀን 2014 (ኢዜአ) የቀድሞ ዳሞታ አትሌትክስ ክለብን መልሶ ለማደራጀት ዓላማ ያደረገ የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ “ኢትዮ- ሰላም ሩጫ በወላይታ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው።
በውድድሩ ሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደኣን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎችና ታዋቂ አትሌቶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
የስፖርት አፍቃሪያን ደጋፊዎችና የተለያዩ የማህበሰሰብ ክፍሎች በሩጫ ውድድር በመሳተፍ ላይ ናቸው።
ሩጫው የሚካሄድበት ዋና ዓላማ የቀድሞው ዳሞታ አትሌቲክስ ክለብን መልሶ ለማደራጀት መሆኑን የአዘጋጅ ኮሚቴው አመላክቷል።
ከጧቱ 1 ሰዓት ከሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ህንጻ ፊት ለፊት ባለው አደባባይ መነሻውን ያደረገው ውድድሩ መድረሻውን ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በማድረግ እየተካሄደ መሆኑ ተመላክቷል