አካታች ብሄራዊ ምክክር ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ የፓናል ውይይት በወላይታ ሶዶ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
አካታች ብሄራዊ ምክክር ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ የፓናል ውይይት በወላይታ ሶዶ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 3 ቀን 2014 (ኢዜአ)አካታች ብሄራዊ ምክክር ላይ ያተኮረ ሀገር አቀፍ የፓናል ውይይት በወላይታ ሶዶ እየተካሄደ ነው።
''አካታች ብሄራዊ ምክክር ለዘላቂ ሰላማችን፣ ለአብሮነታችንና ለብሄራዊ መግባባታችን'' በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የፓናል ውይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ እየተካሄደ ነው።
መድረኩን ያዘጋጁት የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ነው።
በፓናል ውይይቱም በቀጣይ የሚካሄደው ሀገራዊ ምክክሩ የታለመለትን ግብ እንዲመታ ገንቢ ሀሳቦች በማንሸራሸር ግብዓት ይወሰዳል ተብሎ ይጠበቃል።
በመድርኩም ላይ የብሄራዊ ምክክር ፅንሰ ሀሳብ አስፈላጊነት፣ተሞክሮዎች እና ኢትዮጵያ ልትወስዳቸው የሚገቡ ጥናታዊ ፅሁፎች በምሁራን እንደሚቀርቡ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።
የእምነት ተቋማትና የባህላዊ እሴቶቻችን ሚና ለሀገራዊ ምክክር የሚኖረውን ሚና በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ እንደሚቀርብ እንዲሁ ተመላክቷል።
የፓናል ውይይቱን የሚመሩት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደኣ እና የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎ ናቸው።
ለአንድ ቀን በተዘጋጀው በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ የተለያዩ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች፣የፌዴራል እና የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ የህብረሰተብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።